በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ከአዘዞ ጎንደር እያካሄደ ላለው የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ግብአት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ 8000 ሜትር ኪዩብ ዜሮ ቁጥር ጠጠር (aggregate fine) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የዜሮ ቁጥር ጠጠር ግዢ ጨረታ ቁጥር GN-
018/2017
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ከአዘዞ ጎንደር እያካሄደ ላለው የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ግብአት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ 8000 ሜትር ኪዩብ ዜሮ ቁጥር ጠጠር (aggregate fine) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት የመንግስት እቃ ግገዢ ደንብ እና ተያያዥ ህጎች በሚፈቅዱት መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ ብቁ የሆኑ አምራቾች/አቅራቢዎች ለዚሁ ሲባል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው የዲስትሪከቱ ቢሮ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 250000 በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በማይለዋወጥ እና በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ::
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን: ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲስትሪክቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶቻቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያ በአንድ ፖስታ የፋይናንሻል መወዳደሪያቸውን ኦሪጂናልና ኮፒ በማዘጋጀት በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግና በፖስታዎቹ ላይ ስያሜአቸውን በመፃፍ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ መ/ቤቱ ጨረታውን በማንኛውም ምክንያት የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-664988/0925-356890 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
