ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. የተለያዩ ያገለገሉ እና የተጋቡ የምርት ግብዓት ማሸጊያዎች ባሉበት ሁኔታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው ተጫራቾች በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Habesha Breweries S.C. (ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ.)
ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ
ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- HBSC/01/0064/23
ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. የተለያዩ ያገለገሉ እና የተጋቡ የምርት ግብዓት ማሸጊያዎች ባሉበት ሁኔታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው ተጫራቾች በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
|
ተ.ቁ |
ሎት |
ዝርዝር |
ዕቃዎች የሚገኙበት ቦታ |
የሽያጭ ሁኔታ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
ሎት 1 |
የፎርክሊፍት እና የመኪና ጎማዎችን፤ የኤሌክትሪክ ፎርኪሊፍት እና የመኪና ባትሪዎች፤ የመኪና ራዲያተር፤ የእንጨት ፓሊት፤ ቁርጥራጭ ብረቶች፤ ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበሮች |
አዲስ አበባ ጋርመን አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን |
የአንዱ ጊዜ ሽያጭ |
200,000.00 |
|
2 |
ሎት 2 |
ለምርት ግብዓት ማሸጊያነት ያገለገሉ እና የተጋቡ የፕላስቲክ ጀሪካን እና በርሜል፤ ማዳበሪያ፤ ካርቶን |
ደብረ ብርሀን በድርጅቱ ፋብሪካ |
ለአሸናፊው/ዎች ጋር ለአንድ ዓመት በሚፈጸም ውል በየወሩ የሚከናወን ሽያጭ |
100,000.00 |
በመሆኑም ፡-
- አዲስ አበባ ከካርጎ ፊት ለፊት/ከአዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ ፊት ለፊት በሚገኘው ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ዋና መ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- የንብረቶቹን ሁኔታ ከጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለሎት 1 አዲስ አበባ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን እንዲሁም ለሎት 2 ደብረ ብርሃን በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ከጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በድርጅቱ በሚዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሎት 1 ለተዘረዘሩ እቃዎች ብር /200000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም በሎት 2 ለተዘረዘሩ እቃዎች ብር 100000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛኑ ዕለት በ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0911-58 24 80 በመደወል ወይም የጨረታ ሠነዱን በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡-
ቦሌ ከአዲስ የልብ ህክምና ጎን/ካርጎ ፊት ለፊት
አዲስ አበባ
Habesha Breweries S.C
Addis Ababa Ethiopia
Tele 011 662 56 55/011 8694251
Fax 011 663 43 85
PO Box 197 Code 1251
Email info@habeshabreweries.com
ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ
