Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline18 Feb 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Materials

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ጋቢዮን እና የድልድይ ቤሪንግ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል

  • ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ጋቢዮን እና
  • የድልድይ ቤሪንግ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  5. የሚገዛው ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ጋቢዮን እና የድልድይ ቤሪንግ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የአቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ ኦሪጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ይህ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከወጣበት ቀን 26/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 11/06/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጪን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  11. ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን 11/06/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-22-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-3-20-51-55/ 058-2-22-11-07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ፖ.ሣ.ቁ. 382

 

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር

መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

 

Save Tender