በድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፑል በሥሩ ለሚገኙት ለመንገዶች ባለስልጣን ለጽዳትና ውበት ለቄራ አ/ድርጅትና ለአውቶቢስ ክፍል ለ2017 በጀት ዓመት ለከባድና ቀላል መኪኖች የሚሆን ጎማና ካለመዳሪና ፍላፕ እና ለሞተር ሳይክል ተሽከርካሪዎች የጎማ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፑል በሥሩ ለሚገኙት ለመንገዶች ባለስልጣን ለጽዳትና ውበት ለቄራ አ/ድርጅትና ለአውቶቢስ ክፍል ለ2017 በጀት ዓመት ለከባድና ቀላል መኪኖች የሚሆን ጎማና ካለመዳሪና ፍላፕ እና ለሞተር ሳይክል ተሽከርካሪዎች የጎማ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም በግልፅ ጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል። በመሆኑም የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጋብዛችኋል።
በጨረታው መወዳደር ለሚፈልጉ ተሣታፊዎች የጨረታው መስፈርት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ወይም CPO ማስያዝ ይኖርበታል
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ሠነዶች ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀን ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ22ተኛ ቀኑ ይከፈታል፣ የጨረታ ሰነዱን 500 ብር በመክፈል ፋይናንስ ክፍል መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- ጨረታውን ሞልታችሁ የመለሳችሁ እለት በእዛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል 4፡00 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ እንዲሁም በአቅራቢው መሞላት ያለበት የዶክመንት ክፍል ሞልተው ተፈርሞ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ እንድታቀርቡ እያሳሰብን በመመሪያው መሰረት የማያቀርቡ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ማሣሰቢያ፡-መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስ/ቁ 09 15 75 53 24
አድራሻ፡- ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ ትራፊክ መብራት አጠገብ ከቴሌ ህንጻ ከፍ ብሎ።
ድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
