Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
  • Address Lagar, Ras Mekonen Ave, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-551 24 00
  • Websitehttps://eic-et.com/branches/
  • Deadline19 Feb 2025, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)


 

የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሸጥ ይፈልጋል። ጋቢናዎቹን ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ከጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት (ETHOPIAN INSURANCE CORPORATION) ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::

የማስያዣ ዋጋው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ መነሻውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው::

ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፤ ለአሸናፊዎች ግን ሂሣቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ፤ የገዙትን ንብረት ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሳትፎ ያስያዙትን ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ይሰረዛል። ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ።

የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከክፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል።

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ያሸነፈውን ጋቢና በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 439-25-89 እና 011 439-25-45 መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

 

Save Tender