በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በከተማው የውስጥ ለውስጥ ጠጠር መንገድ ግንባታ ማሰሪያ የሚሆኑ የተለያዩ ማሽኖችን መከራየት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
የማሽን ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በከተማው የውስጥ ለውስጥ ጠጠር መንገድ ግንባታ ማሰሪያ የሚሆኑ የተለያዩ ማሽኖችን መከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የኪራዩ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ ዋጋቸውን ሞልተው በክብ ማህተም ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡
- የኪራይ ማሽኖች ዓይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተገለጸው መሰረት የማይመለስ 600.00 /ስድስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለስካቫተር፣ ለግሬደር፣ ሮሎ ማሽኖች ዋጋ ሲቀርብ የሎቤድን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ጠጠሩ የሚገኝበት ርቀት ከደነባ በአማካኝ 8 ኪሎ ሜትር ይሆናል፡፡
- ጠጠር ገልባጭ መኪና 16 ሜትር ኩብ እና በላይ የሚጭን መሆን አለበት፡፡
- ለገልባጭ መኪናዎች የመወዳደሪያ ዋጋ የሚቀርበው በሜትር ኩብ ሲሆን፤ ተጫራች ድርጅት ጠቅላላ ወጪውን የሚሸፍን መሆን አለበት፡፡
- የማንኛውም ማሽኖች የነዳጅ ዋጋ የሚሸፈነው በተጫራቾች ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የማሽን ኪራይ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የተጭበረበረ ሲፒኦ /የባንክ ዋስትና/ ማቅረብ በሕግ ያስጠይቃል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል /የእረፍት/ ቀን ከሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የጨረታው ዋጋ ብር 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/እና በላይ ከሆነ 2% ዊዝሆልድንግ ታክስ ከአጠቃላይ ዋጋ ታስቦ ይከፍላል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ 25% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለማንኛውም መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 410 949/0921 745 220/0925 242 028/0922 461 035 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን
