በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ሞተርሳይክሎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈለጋል፡፡
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2017 የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ሞተርሳይክሎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈለጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 24/2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
- የኤጀንሲው አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ / የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት / ጨፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ ( 3rd Floor ቢሮ ቁጥር03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጩ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30–6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ የካቲት 24/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡30 ሰዓትድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የካቲት 25/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለያንዳንዱ ጨረታ ምናሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ኦሮሚያብሔራዊክልላዊየመንግስትግዥና ንብረትማስወገድኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
CPO ለማሰራት የኦሮሚያብሔራዊ ክልላዊ መንግት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-8340-636
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
ፊንፊኔ
