በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2017 በጀት አመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውል እቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቡድን
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ዕዝ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2017 በጀት አመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውል:-
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የእጅ መገልገያ እና የትምህርትና ስልጠና መርጃ እቃዎች
- ቋሚ የቢሮ እና የቤት (የፈርኒቸር) ዕቃዎች
- የሲቪል አልባሳት
- የማሽነሪ፣ የጀነሬተር፣ ፓምፕ፣ የኦፊስ ማሽን (የኮምፒውተር፣ የፕሪንተር የፋክስ እና የፎቶ ኮፒ) መለዋወጫ እቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚህ መሰረት በተሰማሩበት ስራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓትከጠዋቱ ከ2:30 እስከ 6:00 ሰዓት ከ7:30 እስከ 11:00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐረር ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በሚገኘው ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ጨረታው የካቲት 06/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐረር ቤተ መንግስት መኮንኖች መዝናኛ ክበብ ይከፈታል ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
025 666 85 25/025 466 08 58
098 274 1519/091 565 3530
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
የምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቡድን
ሐረር
