የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የተለያዩ የንብ ቀፎዎች ግዢ ለማድረግ ተጫራቾችን በግዢ መለያ ቁጥር DDAWMEB/GDS/009/2017 በጨረታ አወዳድሮ ውል መግባት ይፈልጋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የተለያዩ የንብ ቀፎዎች ግዢ ለማድረግ ተጫራቾችን በግዢ መለያ ቁጥር DDAWMEB/GDS/009/2017 በጨረታ አወዳድሮ ውል መግባት ይፈልጋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብር 600.00(ስድስት መቶ ብር ብቻ) ከድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማ/ኢነርጂ ቢሮ የግዢ ፋይናንስ ንብረት/አስ/ደጋፊ ስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ቲን ነምበር እና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ጋራንቲ ወይንም (CPO) የጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በሚል ለይተው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ባለው ቅጽ ብቻ ሞልተውና ማህተም አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ20 ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0251-11-13-06
የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
