Tender Detail

Tender Details

  • Company አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ስራ ማኅበራት ዩኒየን
  • Address በአዳማ ከተማ ከአለም ሆቴል ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የዩኒየኑ ቢሮ ከፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ክፍል ፡ አዳማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline12 Feb 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

ድርጅታችን አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ስራ ዩኒየን ዶልፊን ቫን (Dolphin Van) 2006 ሞዴል፣ ሲልቨር ከለር፣ እና ጥሩ ይዞታ ያለውን ተሽከርካሪ በመነሻ ዋጋ ብር 3,600,000.00 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ) ቫትን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድረው መሸጥ ይፈልጋል።

አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ስራ ማኅበራት ዩኒየን


ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ዶልፊን ቫን (Dolphin Van)

የመኪና ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AGFCU...01/2017

 

ድርጅታችን አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ስራ ዩኒየን ዶልፊን ቫን (Dolphin Van) 2006 ሞዴል፣ ሲልቨር ከለር፣ እና ጥሩ ይዞታ ያለውን ተሽከርካሪ በመነሻ ዋጋ ብር 3,600,000.00 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ) ቫትን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድረው መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

    1. በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትርበስራ ሰዓት በአዳማ ከተማ ከአለም ሆቴል ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብለው በሚገኘው የዩኒየኑ ቢሮ ከፋይናንስ እና ንብረት አስተዳድር ክፍል በአካል በመገኘት በማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
    2. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በድርጅቱ ህንፃ ፓርኪንግ ቦታ ቀርቦ መመልከት ይችላሉ።
    3. ተጫራች ድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ማቅረብ አለበት። የሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን መግለፅ አለበት።
    4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የሞሉትን ዋጋ 5% በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምረው ለ15 ቀናት አየር ላይ በመቆየት በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በ8:30 የሚከፈት ይሆናል።
    6.  በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ለዩኒየኑ ገቢ ይደረጋል።
    7.  ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አብዲ ጉዲና ኃ/የተ/ የፋይናንስ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን

 

Save Tender