በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም በተገኘ በጀት ሎት 1 በጊሚሴ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ ሎት2 በሶለቄ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ /MHM/ ከፍል ግንባታ፣ ሎት 3 የወረዳው ትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽ/ቤት ከሱተን ዙሪያ-ውድገት ገፈርሳ ባለው ዩራፐ መንገድ ላይ slap culvert. checkdam, drifit እና ford ጥገና ስራ /የጉልበትና የማቴሪያል አቅርቦት ጨምሮ/ ሎት 1 እና ሎት 2 በግንባታ ዘርፍ ፈቃድ ባላቸው GC/BC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ሎት 3 GC/RC ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ በሆኑ አካላቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-05/2017
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም በተገኘ በጀት ሎት 1 በጊሚሴ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ ሎት2 በሶለቄ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ /MHM/ ከፍል ግንባታ፣ ሎት 3 የወረዳው ትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽ/ቤት ከሱተን ዙሪያ-ውድገት ገፈርሳ ባለው ዩራፐ መንገድ ላይ slap culvert. checkdam, drifit እና ford ጥገና ስራ /የጉልበትና የማቴሪያል አቅርቦት ጨምሮ/ ሎት 1 እና ሎት 2 በግንባታ ዘርፍ ፈቃድ ባላቸው GC/BC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ሎት 3 GC/RC ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ በሆኑ አካላቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ቲን ነምበር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- ጨረታው የሚቆየው ከ20/05/2017 ዓ.ም እስከ 10/06/2017 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በሁለት ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ በመሙላት ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11/06/2017 ዓ.ም ሎት 1 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ በ8:30 ይከፈታል። ሎት 2 8፡30 ሰዓት ታሽጎ 9:00 ይከፈታል፡፡ ሎት 3 9:00 ሰዓት ታሽጎ 9:30 ሰዓት ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት የግ/ከ/ን አስ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከሎት 1-3 ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስኪ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈጽም በግዢ መመሪያ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- በአፈጻጸም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- በወረዳው ውስጥ ፕሮጀክት ይዘው 75% እና ከዚያ በላይ መድረሱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከአሰሪው መ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ሰነድ ላይ ሀሰተኛ ሰነድ ቢገኝ ከጨረታ ሂደት ውጪ ተደርጎ በህግ ተጠያቂ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የግንባታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ለሎት 1 እና 2 ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት 3፣ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ:- 046-8-83-05-33/128
በማ/ኢ/ክ/መ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
