በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ማለትም፤
ሎት 1 ስቴሽነሪ
ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ
ሎት 3. ለቢሮ አገልግሎት ጄኔሬተር
ሎት 4. ሞተር ሳይክል
ሎት 5. የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ
- የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1. 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2. 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት 3. 5000 /አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት 4. 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/፣ ለሎት 5. 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ፣ ካሽ ወይም ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ሰነድ ከምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የማይመለስ 200 ሁለት መቶ ብር ከፍሎ በመውሰድ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ ለየ ብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 የስራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ዋጋዎች በግልጽ የሚታይ መሆን አለበት ወይም ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ቀን አይቀይርም፡፡
ለበለጠ መረጃ :- 09-25-10-92-00/09-29-94-72-57/09-29-93-89-04/0939 33 08 29
በማዕ/ኢት/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ
ስልጢ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
