በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ የሚከተሉትን አገልግሎት እና እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር :- ECC-MOJ/NCB/04/2017 እና ECC-MOJ/NCB/05/2017
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ የሚከተሉትን አገልግሎት እና እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
1. የግዥ መለያ ቁጥር :- ECC-MOJ/NCB/04/2017
* ሎት 1፡- ደረጃውን የጠበቀ የታሸገ ግማሽ (1/2) ሊትር ውሃ፣
* ሎት 2፡- ዘመናዊ ለሱፍ ማላባሻ የሚሆን የሴቶች ቆዳ ጫማ፣
2. የግዥ መለያ ቁጥር :- ECC-MOJ/NCB/05/2017
* ሎት 1፡- የተለያዩ አይነት ሞዴል መኪኖች ጥገና አገልግሎት፣
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር የተዛመደ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር (egp) ውስጥ የተመዘገቡና የተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የታሸገ የመጠጥ ውሃ ተወዳዳሪዎች ከጤና ሚኒስቴር የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታሸገ የመጠጥ ውሃ ተወዳዳሪዎች በኢትዮጵያ ጥራትና ቁጥጥር ኤጄንሲ ባለስልጣን ለአምራቹ የተሰጠ ሰርተፊኬት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታሸገ የመጠጥ ውሃ ተወዳዳሪዎች ከኢትዮጵያ የምግብ፣ መድሃኒት እና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በተሰማሩበት ዘርፍ ለአምራቹ የተሰጠ ሰርተፊኬት ስድስት ወር ያላለፈው መሆኑን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታሸገ የመጠጥ ውሃ ተወዳዳሪዎች Certificate of Analysis for drink water ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ መሿለኪያ አካባቢ ይርጋ ሃይሌ ፕላዛ ከሚገኘው የኮሚሽኑ ዋ/መ/ቤት የግዢ ቡድን አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን እንደ ስራ ቀን ተቆጥሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ድረስ ከ4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት በኮሚሽኑ ዋ/መ/ቤት የግዢ ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- ሰነዱ በሚላክበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት፣ ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃው መያያዝ አለበት፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) CPO ወይም ባንከ ጋራንቲ በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በከፍል ሁለት ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO or Bid Bond Guarantee በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ የጥቃቅን እና አነስተኛ የድጋፍ ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ያስገቡ ናሙናዎቹንም ለግዥ ክፍል ማስረከብ አለባቸው:: ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ለውድድር አይቀርብም።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር :- 022-2-36-13-14/09-24-07-70-78
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
