የፍርድ ባለመብት ምሳነሽ ግርማ እና የፍርድ ባለእዳዎች መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክ/ከተማ ሆራ አርሰዴ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ቤት በጨረታ እንዲሸጥ ፍርድቤቱ አዟል።
በቢሾፍቱ ከተማ ከ/ፍ/ቤት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ መደበኛ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለመብት ምሳነሽ ግርማ እና የፍርድ ባለእዳዎች 1ኛ.አቶ ትሁት ማሞ 2ኛ ወ/ሮ የትናየት ማሞ 3ኛ. ወ/ሮ መራዊት ማሞ መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር አስመልክቶ ፍ/ቤቱ በ07/05/2017 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክ/ከተማ ሆራ አርሰዴ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 125 የሆነ አዋሳኙ በምስራቅ አቶ አሰፋ አበበ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን መንገድ፣ እና በደቡብ መንገድ አቶ አበበ ለማ የሚዋሰነውን በጨለለቃ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በቀን 08/1/2016 ዓ.ም ግምት መሰረት 3,468,877.19 (ሶስት ሚሊየን አራት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ሰባት ብር ከ19/100 ሳንቲም) ዋጋ መነሻ በሆነ በቀን 14/06/2017 ዓ.ም ጠዋት ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ግልጽ በሆነ ጨረታ ተሸጦ ውጤቱ እንዲቀርብ እና የጨረታው ተሳታፊ 1/4 ሲፒኦ እንዲያስይዙ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በቢሾፍቱ ከተማ ከፍ/ቤት የጨለለቃ ከተማ ወ/ፍ/ቤት
