በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ጽ/ቤት ከዚህ በታች አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የሃይብሪድ ቴክኖሎጂ ዩፒኤስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የኮምፒውተር ወረቀትና አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የሃይብሪድ
ቴክኖሎጂ ዩፒኤስ ግልጽ ጨረታ
የግዥ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ ደብ/ሪጂ/ግ/ጨ/001/2017
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ጽ/ቤት ከዚህ በታች አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የሃይብሪድ ቴክኖሎጂ ዩፒኤስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የቢሮ መገልገያ እቃዎች |
የጨረታ ዋስትና |
የሚዘጋበት ቀን |
የሚከፈትበት ቀን |
|
1 |
የኮምፒውተር ወረቀትና አላቂ የቢሮ እቃዎች
|
65,612.00 |
የካቲት 01 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 |
|
2 |
የሃይብሪድ ቴክኖሎጂ ዩፒኤስ 3.0 kw
|
100,000.00 |
የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30
|
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ደብረ ብርሃን ሪጅን ከሚገኘው አፄ ዘርአያቆብ ህንጻ ላይ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 308 የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ከ00/100) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በማድረግ በሰም በታሸነ ኤንቨሎፕ እስከ የካቲት 01/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሪጅኑ ሰፕላይ ቼይን፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 308 የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ሎት-1 ብር 65,612.00 (ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አስራ ሁለት ብር ብቻ)፣ ሎት-2 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል “ኦሪጅናል እና ኮፒ” እና ፋይናንሻል “አሪጅናል እና ኮፒ” በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ደብ/ሪጂ/ግ/ጨ/001/2017 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 308 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-13-20-50-52 / 011 637 60 94/ መደወል ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ጽ/ቤት
