የወልቂጤ አፈር ምርመራ ማዕከል ለአፈር ምርመራ የሚሆኑ የተለያዩ ማሸነሪዎች ማለትም ፡- Shaker Orbital, PH meter, Analytical balance, Spectro Photo Meter, Glass Wares የመሳሰሉ ማሽነሪዎችና እንዲሁም ፈሳሽና ጠጣር ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የወልቂጤ አፈር ምርመራ ማዕከል
የእቃ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የወልቂጤ አፈር ምርመራ ማዕከል ለአፈር ምርመራ የሚሆኑ የተለያዩ ማሸነሪዎች ማለትም ፡- Shaker Orbital, PH meter, Analytical balance, Spectro Photo Meter, Glass Wares የመሳሰሉ ማሽነሪዎችና እንዲሁም ፈሳሽና ጠጣር ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ፡-
- የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የግብር የከፈሉ፤
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው በአቅራቢዎች ሥም ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፣
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ አፈር ምርመራ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 5 ህጋዊ ፈቃዳቸውን በመያዝ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያስረዳ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ወልቂጤ አፈር ምርመራ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው::
- ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ በኋላ 15ኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ አልያም የህዝብ በአል ከሆነ የመክፈቻ ቀን ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልከ ቁጥሮች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ስልከ ቁጥር 0113300866 ወይም 0912004605
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የወልቂጤ አፈር ምርመራ ማዕከል
