የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 1/3 ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ሻሸመኔ ከተማ 150,000 ኩንታል ስኳር እንዲጓጓዝለት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመዋዋል የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/22/SIG/2017
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 1/3 ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ሻሸመኔ ከተማ 150,000 ኩንታል ስኳር እንዲጓጓዝለት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመዋዋል የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊና ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ/ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወይም በኢትየጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣
ፈሊፒስ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 5 50 04 17 ወይም 011 5 51 62 71
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው አድራሻ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
