ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው ከሲሪ ከቢር ሀሚድ ከዳንሼ-ዱላሞይ፤ ከቦልጫመኝ ገሬኖ ባለው አዲስና ነባር መንገድ ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር GGWW/0018/2017
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው ከሲሪ ከቢር ሀሚድ ከዳንሼ-ዱላሞይ፤ ከቦልጫመኝ ገሬኖ ባለው አዲስና ነባር መንገድ ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቶች
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 100,000 (መቶ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ።
ማሳሰቢያ ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም ።
- በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ሳይወስድ ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል።
ለበለጠ መረጃ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ
መሀል አምባ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
