Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462129501
  • Website
  • Deadline06 Feb 2025, 3:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply

በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2017 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/17

 

በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2017 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • LOT 1. የአባላዘር ላብራቶሪ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች፣
  • LOT 2. የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች እና
  • LOT 3. የእንስሳት መኖ (ድርቆሽ ሳር/ ቦንዳ ሳር) በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በስፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ስዓት ድረስ የቴከኒካል እና የፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያዳንዳቸው በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO ቴክኒካል ዶከሜንት ውስጥ በማድረግ አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጊዜ ወይም በቦታው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።

 

ማዕከሉ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር 0462129501/ 0462129504 ይደውሉ፡፡

 

   የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ ፣

ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል

ሀዋሳ

Save Tender