በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ሎት 1/ ደንብ ልብሶች ሎት/2 የጽዳት እቃዎች ሎት/3 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት/ 4 ልዩ ልዩ እቃዎች ሎት/5 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሎት/6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት ሎት/7 የሕትመት ስራ ሎት/8 መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ ሎት/10 የፈርኒቸር ጥገና ሎት /11 ቋሚ እቃዎች ሎት /12 የጉልበት ስራ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2017
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ሎት 1/ ደንብ ልብሶች ሎት/2 የጽዳት እቃዎች ሎት/3 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት/ 4 ልዩ ልዩ እቃዎች ሎት/5 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሎት/6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት ሎት/7 የሕትመት ስራ ሎት/8 መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ ሎት/10 የፈርኒቸር ጥገና ሎት /11 ቋሚ እቃዎች ሎት /12 የጉልበት ስራ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቲን ያላቸውና በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቲን (TIN) ሰርተፍኬት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችል ይሆናል። ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች በቅድሚያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) የሚጫረቱበት ሎት/1 የደንብ ልብሶች ግዢ ብር 2500 ሎት/2 የጽዳት እቃዎች 2200 ሎት/3 አላቂ የቢሮ እቃዎች 2000 ሎት/4 ልዩ ልዩ እቃዎች 1000 ሎት/5 የኤሌክትሮኒከስ ጥገና 3000 ሎት/6 እና የጭነት አገልግሎት 4000 ሎት 7 የህትመት ስራ 3000 ሎት/8 የመስተንግዶ አገልግሎት 2300 ሎት/9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ 2000 ሎት/10 የፈርኒቸር ጥገና 2300 ሎት /11 ቋሚ እቃዎች 1500 ስራ ሎት 12 /የጉልበት ስራ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት እና በማሸግ ከጨረታዉ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ኮ/ቀ/ክ/ወ/07 ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል ይህ ቀን የበዓል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም እንዲሁም አማራጭ ይዞ መቅረብ አይቻልም፡፡
- በግዥ አዋጁ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ስለመደራጀታቸው የሚገልፅ ከአደራጃቸዉ ተቋም በጽ/ቤቱ ኃላፊ የተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- የአንዱ ዋጋ የማይለወጥ በመሆኑ ተጫራቾች በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም የዕቃዉ ጥራትና ዋጋ ከግምት በማስገባት እንዲሞሉ።
- የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዉ ወረዳዉ እስቶር (ዕቃ ግምጃ ቤት) ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆኑን ከግንዛቤ ዉስጥ እንድታስገቡ፤
- የዕቃዉን 20 ፐርሰንት መጨመር ወይ ወይም መቀነስ መ/ቤቱ የሚችል መሆኑን እና ጠቅላላ ዋጋዉን 25 ፐርሰንት 6 ወር ድረስ ጨምሮ ሊይዝ የሚችል መሆኑን፤
- ተጫራቹ ለተወዳደሩባቸዉ ሎቶች ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነዉ፡፡
ማሳሰቢያ ፡- የጉልበት ስራ ለሚወዳደሩት በስራ እድል ፈጠራ የተደራጁ ቢሆን ደብዳቤ እና የቲን ቁጥር ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አድራሻ ፡- ኮ/ቀ/ክ/ክ/ወ/ 07 ቤቴል እሳት አደጋ ፊት ለፊት በ40 ሜት ሜትሩ መንገድ በኩል ነዉ
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር ፡- 0113696634 ይደውሉ፡፡
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07
አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
