የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ ቀደም ሲገለገልባቸው የነበሩ በርካታ ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በስክራፕ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና
ማሽነሪዎች እና ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች
(Auxillary Equipments) በቁርጥራጭ ብረትነት ለመሸጥ
የተዘጋጀ የሽያጭ ጨረታ ቁጥር ንብ/001/2017
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ ቀደም ሲገለገልባቸው የነበሩ በርካታ ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በስክራፕ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
- ተጫራቾች ሊያሟላቸው የሚገቡ የቅድመ ሁኔታ (ህጋዊነት ያላቸው ሰነዶች)
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት (trading license) (ለ2017 የታደሰ)
- የታክስ ከፋይ ሰርተፍኬት (Tax Payer identification Certificate)
- የብረታ ብረት ማቅለጫ ድርጅት መሆንን የሚያረጋግጥ የብረት አቅላጭነት ሰርተፍኬት
- የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (Value Added Tax Registration Certificate)
- ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታከስ ክሊራንስ (Tax Clearance)
- በየመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት (online)
- በየትኛውም የመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ (debar) ስለመሆናቸው ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ማረጋገጫ ደብዳቤ፡፡
- ተቀባይነት ያለው የስልጣን ውክልና (Power of attorney)
- ተቀባይነት ያለው የጨረታ ማስከበሪያ
- የተፈረመ የተጫራቾች ያለማጭበርበር ቃል የገቡበት ቅጽ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን የሚሳተፉት በአሽሙር ሽርክና ከሆነ የአሽሙር ሽርከና ስምምነታቸውን (JV Agreement or intent) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአሽሙር ሽርክና የሚጫረቱ ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1 ስር የተዘረዘሩትን መለኪያዎች በተናጠል ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡
- ተጫራቾች የ2016 ዓ.ም በኦዲተር የተመረመረ የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአሽሙር ሽርክና የሚጫረቱ ተጫራቾች ሁለቱንም የባንክ የሂሳብ መግለጫ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለዚህ ጨረታ ብቁ የሚሆነው 2016 ዓመታዊ ሽያጭ (annual turnover) ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ነው፡፡
- በአሽሙር ሽርክና የሚጫረቱ ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 5 የተጠቀሰውን መመዘኛ በጋራ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች በተጫረቱበት ዋጋና የብረት (scrap) መጠን ልክ ክፍያውን ለመፈጸም የሚችሉ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የጥሬ ገንዘብ ማሳያ የጨረታ ሰነዱን እስካስገቡበት ቀን ድረስ ያለ ባንክ ስቴትመንት ወይም ከታወቀ ባንክ ጨረታውን ካሸነፉ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ብድር የሚሰጧቸው መሆኑን ማረጋገጫ (Unconditional Credit facility) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በአሽሙር ሽርክና ሚጫረቱ ከሆነ ከላይ በተራ ቁጥር 7 የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በጋራ ወይም በተናጠል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የሽያጭ ጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በድርጅታችን ፋይናንስ መምሪያ ገቢ በማድረግ ከንብረት አስተዳደርና ቡድን መሪ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪ፣ ተሽከርካሪ፤ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ባሉት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ጊቢ /ቃሊቲ ቶታል አካባቢ/ እና ወርቁ ሠፈር በሚገኘው በኢንተርፕራይዙ ጊቢ በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዝቅተኛ ሊገዛ የሚገባው 1,000,000 ኪ/ግ ቁርጥራጭ ብረቶች ሆኖ በከፊል ወይም በጥቅል መጫረት ይችላል፣
- የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪ፣ ተሽከርካሪ፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ስክራፕ ሽያጭ የጨረታ ማስከበሪያ በጥቅል ብር 100,000.00 አንድ መቶ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO በድርጅታችን ትክክለኛ ስም መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሚል አሰርተው CPO ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፤
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ስልክ ቁጥር /011-4-40-34-34 ማዞሪያ 011-4-42-22-70/71/72
E-MAIL አድራሻ Info @dce-et.com
የድረ ገፅ አድራሻ WWW.dce et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 114-40-04-71 / 0114-42-07-46
አድራሻ ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) እንገኛለን፡፡
ድረ ገፅ:-www.dce.et.com
ኢሜል:- INFO @dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
