Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
  • Address ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 57 42
  • Websitehttps://aarevenuesbureau.gov.et/
  • Deadline29 Jan 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Generators

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር: 007/2017

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

• ሎት አንድ - Scanning machine

• ሎት ሁለት - ዲጂታል ማስታወቂያ

• ሎት ሶስት - የሜትር ታክሲ አገልግሎት

• ሎት አራት - አውቶማቲክ ጄኔሬተር

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦሪጅናል ኮፒ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር" "አንድ ኦሪጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 2% ፣ ለሎት ሁለት 2%፣ ለሎት ሶስት 2%፤ ለሎት አራት 10,000.00፤ የሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ C.P.O ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: CPO መሰራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ /ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለጸ ከሆነ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራች በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በተገለፀው ቀን ቀርቦ ውለታ ካልፈፀመና የውል ማስከበሪያ ካላስያዘ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

➢ በስልክ ቁጥር 0115 57 57 42/0115 57 19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

 

Save Tender