በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 035/2017
በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት -
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 035/17 በ19/05/2017 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ስለዚህ ለጨረታ የቀረበውን ተሽከርካሪዎች ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች:-
- ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ
- ለጨረታ የቀረበው ተሽከርካሪ የሚገኘው ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ ነው::
- በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ 6 ሰአት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና ሪሲት በመውሰድ ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡
- ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ጉምሩክ ሙድአነኖ የሚገኘው ግቢ ነው::
- ተጫራቾች በተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት ::
- ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ለመግዛት በሞሉት ዋጋ ልክ ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ንግድ ባንክ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና CPO እንዲሁም የታደሰ መታወቂያ በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 ድረስ በድሬዳዋ ጉምሩክ ሙድአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከጠዋቱ 3፡50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ጉምሩክ ሙድአነኖ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ፖስታ አንቀበልም ::
- ለግልጽ ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ወኪሎቻቸው በጨረታው ቦታው ላይ ባይገኙም ጨረታ ሳጥን በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላት ላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 13 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ በባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
- በግልጽ ጨረታ ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ሥም መሞላት አለበት፡፡
- ተጫራቹ ዋጋ ለሰጠው የብር መጠን በቁጥር እና በፊደል መፃፍ አለበት ስርዝ/ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጉምሩከ ኮምሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 025-1-12-49-28 ( 0911953903) መደወል ይቻላል ::
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
