Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address ደ/ብርሃን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline22 Feb 2025, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአፈ/ከሣሾች እነ ህጻን ሳሙኤል ነጋሽ (9ሰዎች) እና በአፈ/ተከሣሽ ንጉሴ ገ/ጻዲቅ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር-ጉዳይ የሟች ደበበ ገ/ጻዲቅ ንብረት የሆነው ቤትና ቦታ በሰላድንጋይ ከተማ 01 ቀበሌ ጻድቃኔ ጎጥ ከምስራቅ ዘበነ ንጋቱ ፣ በምዕራብ ሸዋበረ ፣ ከሰሜን ግዛው ወንድምሁን እና ከደቡብ መንገድ አዋሣኝ የሚገኘው 250 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን ቤት በዜሮ መነሻ ዋጋ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት በጨረታ እንዲሽጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

                                                                                                

በአፈ/ከሣሾች እነ ህጻን ሳሙኤል ነጋሽ (9ሰዎች) እና በአፈ/ተከሣሽ ንጉሴ ገ/ጻዲቅ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር-ጉዳይ የሟች ደበበ ገ/ጻዲቅ ንብረት የሆነው ቤትና ቦታ በሰላድንጋይ ከተማ 01 ቀበሌ ጻድቃኔ ጎጥ ከምስራቅ ዘበነ ንጋቱ ፣ በምዕራብ ሸዋበረ ፣ ከሰሜን ግዛው ወንድምሁን እና ከደቡብ መንገድ አዋሣኝ የሚገኘው 250 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን ቤት በዜሮ መነሻ ዋጋ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት በጨረታ እንዲሽጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

በመሆኑም :-

  1. ገዥው /ተጫራቹ/ ያሸነፈበትን 1/4ኛ ገንዘብ ወዲያውኑ ለሐራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው::
  2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው፡፡
  4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ከላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሐራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
  5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

 

 

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ደ/ብርሃን

 

Save Tender