Tender Detail

Tender Details

  • Company Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)
  • Address ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት አጠገብ ዋስትና የንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-11-23-13
  • Websitehttps://psssa.gov.et/
  • Deadline26 Jan 2025, 10:15 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle (Garage Service)

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት የፅዳት እቃ እና የጋራጅ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)


 

ግልፅ  ጨረታ ማስታወቂያ

 

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት የፅዳት እቃ እና የጋራጅ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  3. ተጫራቾች ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ያላቸው፤
  4. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ 60 ቀናት ይሆናል፤
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ዋስትና ንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ በመምጣት የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሠነድ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ዋስትና ንግድ ማዕከል ግራውንድ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በ 8ኛው ቀን 4፡15 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ይከፈታል፡፡ 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ4፡15 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ይከፈታል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡- የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡

አድራሻ ፡- ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት አጠገብ ዋስትና የንግድ ማዕከል ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-23-13

 

 

የመንግስት  ሠራተኞች  ማኅበራዊ  ዋስትና  አስተዳደር

 

Save Tender