በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ መጠኑ 1,774.53 ኩ/ል 1ኛ ደረጃ ምስር በአዳማ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ መጠኑ 1,774.53 ኩ/ል 1ኛ ደረጃ ምስር በአዳማ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
እህሉ የሚገኝበት ቦታ |
የእህል ዓይነት |
መጠን በኩ/ል |
የጥራት ደረጃ |
እህሉ የሚገኝበት መጋዘን |
እህሉ የሚውለው አገልግሎት |
|
1 |
አዳማ |
ምስር |
1,774.53 |
1ኛ ደረጃ |
9 |
ለሰው ምግብነት |
|
ድምር |
1,774.53 |
|
|
|
||
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- አግባብነት ያለው በጥራጥሬ በጅምላና ችርቻሮ ንግድ ወይም ላኪነት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- ምስሩን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት እህሉ በሚገኝበት መጋዘን በአዳማ መጋዘን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 – 6፡00 እና ከሰዓት 7፡00 – 10፡30 እና ቅዳሜ ከ2፡00 - 6፡00 በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በዘርፉ ስም (የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ ወይም Grain and Coffee Trading Business Unit) በሚል ብቻ የተሠራ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፤
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ያለስርዝ ድልዝ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በግልፅ የማይነበብ ትክክለኛውን የዋጋ አቀራረብ ሥነ ስርዓት ያልተከተለ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ የሚደረግ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ያስፈልጋል።
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥር 4/2017 ዓ.ም በማለት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 004 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። አስራ አንደኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ውል ሲፈርም የውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ መቻል አለበት፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 004 ይከፈታል። አስራ አንደኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት እህሉን ተረክቦ ወደሚፈልግበት ቦታ በራሱ የሚያጓጉዝ ይሆናል።
- ዘርፉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 66 47 45 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
