የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፍትህ ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማ/ዕ/ኢ/ክ/መንግስት ግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፍትህ ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሎች ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመስሪያ ቤቱ ግዢ፣ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ያቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት/ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና (Sample) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸው ዕቃዎች መስሪያ ቤታችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀን ድረስ የፀና ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 556 2550/0916 239 206/0911 781 396 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
በማ/ዕ/ኢ/ክ/መንግስት ግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ሀላባ
