በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለድጉና ፋንጎ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በ2017 በጀት ዓ.ም በሴፍትኔት ካፒታል ለግዥ ከተላከው በጀት የተለያዩ ፍራፍሬ እና የችግኝ ዘር፤ ፖሊቴን ቲውብ፣ የመጠጥ ውሃ ዕቃ፤ የተለያዩ ህንጻ መሳሪያ፤ የተለያዩ የእንጨት አይነቶች፤ በናፍጣ የሚሰሩ ጀነሬተሮች፤ የተለያዩ የማዕድን ውጤቶች እና የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ

ሎት 1 የተለያዩ ፍራፍሬ እና የችግኝ ዘር
ሎት 2 የተለያዩ ፖሊቴን ቲውብ አይነቶች
ሎት 3 የተለያዩ የህንጻ መሳሪያ
ሎት 4 የተለያዩ የማዕድን ውጤቶች
ሎት 5 የተለያዩ የእንጨት አይነቶች
ሎት 6 በናፍጣ የሚሰሩ ጀነሬተሮች
ሎት 7 የተለያዩ የመጠጥ ውሃ ዕቃዎች
ሎት 8 የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች
በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ቫት፤ ቲን እና አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው ::
- 2% ለመንግሥት ግብር እንደሚቆረጥ ማወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋኢል ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 13 ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱን ሎት በባንክ የተረጋገጠ 10,000 /አስር ሺህ ብር ሲፒኦ /በጥሬ ማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥለው በሚውለው 16ኛ ሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች እለቱ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0916 719 903/0966 523 551/0916 114 241/
በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ቢጠና