የአስረሐዋርያት ት/ቤት የተማሪዎች የአስተዳደር ሰራተኞች ሽንት ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ግንባታውንና ተያያዥ ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል።
የአስረሐዋርያት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡ አ\ሐ\ት\ቤት\01/2017
የአስረሐዋርያት ት/ቤት የተማሪዎች የአስተዳደር ሰራተኞች ሽንት ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ግንባታውንና ተያያዥ ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል።
- በጨረታ መወዳደር የሚችሉት
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ክሊራንስ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሟልተው ማቅረብ የሚችሉ እና እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( unconditional bank guaranty) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 9፡00 ሰዓት ከት/ቤቱ ቢሮ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል፣ የፋይናንሺያል እና የጨረታ ማስከበሪያ ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን በተለያዩ ሶስት ፖስታዎች አሽገው የተጫራቾች ፊርማ እና ማህተም በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ አርፎባቸውና ኦርጅናል ተብሎ ተፅፎባቸው በአንድ እናት ፖስታ ተጠቃለው ለኦርጅናል ስነዱ በተዘጋጀው ሳጥን መግባት አለበት፡፡ እንዲሁም የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ፎቶ ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ ሁለት ሰነዶች ታሽገው የተጫራቾች ፊርማ እና ማህተም አርፎበት በአንድ እናት ፖስታ ተጠቃለው ለኮፒ ሰነድ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መግባት አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ቆይቶ በ5ኛ ቀን በዕለቱ ዓርብ ጥር 17 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8 ሰዓት ታሽጎ በዛው ዕለት ከቀኑ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ :- ዊንጌት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ
ስልክ ፡- 0912 430 173, 0912 034 444, 0910 043 039
የአስረሐዋርያት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
