Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0113290317
  • Website
  • Deadline30 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ሞተሮች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ለሶስተኛ  ጊዜ  የወጣ  ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ሞተሮች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም፡- ሎት 1 የተለያዩ ሞተሮች

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት1 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸው ዕቃዎች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በእያንዳንዱን ሎት የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶክመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ክ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸዉ፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸዉን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለዉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል:: ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ ከ8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ቀኑ 8፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ አለመገኘት ጨረታዉ ከመከፈት አያስተጓጉለዉም፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  12. ተጫራቾች የተጫረቱባቸው ሞተሮች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው::
  13. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  14. ማሳሰቢያ :- ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው::

 

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 0113290317/011 329 03 18/011 329 02 60/011 329 00 06

 

በማዕከላዊ  ኢትዮጵያ  ክልላዊ  መንግስት  በጉራጌ  ዞን  የእዣ  ወረዳ  ፋይናንስ  ጽ/ቤት

 

Save Tender