በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳዉሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ያገለገሉ መኪናዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የዳውሮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የዳዉሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ያገለገሉ መኪናዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ማስታወቂያ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማሟላት ያለባቸው
- በማንኛዉም የስራ መሰክ የተሰማሩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሠነድ የሚሸጠው በዳ/ዞ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያ ፈጽሞ በ20 ቀናት ዉስጥ ማንሳት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ክፍያውን እንደፈፀሙ ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት/ CPO / ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደ/ም/ ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ዳዉሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በግዥ ፋይናንስ ሥም በተከፈተው አካውንት 1000042591703 ላይ ገቢ በማድረግ ከግዥ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 21 ላይ ለዚሁ አገ/ት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል መወዳደር ይችላል፣
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሠነድ ላይ ፤ ሥማቸዉን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸዉን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት የሚችሉት በመ/ቤታችን በተዘጋጀዉ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ መኪና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ጥሬ ገንዘብ በኦርጅናል ዶክመንት ፖስታ ውስጥ በማድረግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ያስያዙት /CPO/ ለወደቁት ሲመለስ ለአሸናፊዎች ግን መኪናውን አንስቶ ሲጨርሱ ይመለሳል፣
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጨራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የዋጋ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፣
- የጨረታ ሥራን ሆን ብሎ ከጨረታ ማሸጊያ ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻዉ የጨረታ ሥነ-ሥርዓትን ማወከና መረበሽ ከዉድድር ዉጪ ያደርጋል ፣ በህግም ያስቀጣል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጐ በዕሉቱ 4፡30 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ም/ኢ/ህ/ ክልል ዳዉሮ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መከፈቻ ሥነ ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ በስቁ 0473450613 /0917516231/ 0917008736/ይደውሉ፡፡
ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የዳውሮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
