አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፀውን የአገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አአከአአድ/ግጨ/ተሽእሌፅአገ/005/2017
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፀውን የአገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የአገልግሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የተሽከርካሪ እጥበት እና የሌሎች ፅዳት አገልግሎት ግዥ |
ብር 50,000.00 |
ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት |
ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት |
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ፡-
- ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውንና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ወቅታዊ ደብዳቤ (Tax Clearance) በኦላይን የመንግሥት ግዥ አቅራቢዎች ዝርዝር (https://www.egp.ppa.gov.et) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT Registration) እና የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት (TN Certificate) ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመያዝ 22 እየሩስ ህንፃ 7ኛ ፎቅ አዲስ አበባ ከተማ የአውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7- 02 መውሰድ የሚችሉ ሆኖ የጨረታው ሰነድም በዚሁ አድራሻ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሰንጠረዡ የተገለፀውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት ሲሆን ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ተጫራቾች የታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካልና ፋይናሻል ሰነድ በአንድ ፖስታ ሆኖ ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ መቅረብ ያለበት ሲሆን፤ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ፖስታዎቹ ላይ መገለጽ አለበት።
- የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን የሚመለከት መረጃ በስልክ ቁጥር 0118-21-22 14 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
