የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን መንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደር አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- ሲ/መ/ባ/025/2017
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን መንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደር አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የሎቶች ዝርዝር |
የፕሮጀክት ስም |
በክልሉ ውስጥ መንገድ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
|
1 |
ሎት 1 |
አባያ ወታራ ጋንደ |
ወንዶ ገነት |
6 |
|
2 |
ሎት 2 |
ጃራዳዶ ባሌላ መገንጠያ |
ደሬ ባፋኖ |
10.5 |
|
ባሌላ መገንጠያ ዳራራ ጩኮ |
ቦርቻ/ዳራራ |
15 |
||
|
ሀዌላ ለኩ ይርጋዓለም |
ሸባድኖ ዳለ |
15 |
||
|
3 |
ሎት 3 |
ዝግባ መገንጠያ ሎካ አባያ |
ዳሌ/ ሎካ አባያ |
15 |
|
አዋዳ ሳሳሞ አላታ ወንዶ |
ዳሌ |
5 |
||
|
ወንሾ ሳሳሞ ዴላ |
ዳሌ |
|
||
|
4 |
ሎት 4 |
አላታ ወንዶ አላታ ጩኮ |
አላታ ወንዶ/ አላታ ጩኮ |
6.6 |
|
ጋርብቾ ኪላ 2ተኛ ሞግሳ |
አላታ ወንዶ |
5.3 |
||
|
5 |
ሎት 5 |
ሀገር ሰላም ጋታማ |
ሁላ |
8.3 |
|
ቃባዶ አባራ ሁላ |
ሁላ ዳራ ኦትልቾ |
9 |
||
|
ሽልቾ አባራ ሁላ |
ዳራ ኦትልቾ |
13.5 |
||
|
6 |
ሎት 6 |
ጠጢቻ ቡርሳ ያዬ |
ቡርሳ |
12 |
|
ሻንታዌኔ ዳላቻ ቡራ |
ባንሳ/ ቡራ |
12 |
||
|
ያዬ ሚቅቾ |
አርበጎና |
9 |
||
|
ባንሳ ዋሬ ቡራ |
ባንሳ/ ቡራ |
7 |
||
|
7 |
ሎት 7 |
መጆ ዳኤለ |
አሮሬሳ/ ዳኤላ |
10 |
|
መጆ ግርጃ |
አሮሬሳ/ ዳኤላ |
9 |
||
|
8 |
ሎት 8 |
ጭሬ ላሌሳ ጉቦ ሔማ |
ጭር |
14 |
በዚሁ መሠረት ፡-
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የማከራየት ፈቃድ ያላቸው ወይም በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው የሆኑ፤
- ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደር የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ፣ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም 14m3 የሆነ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አዲስ ስራ ፈቃድ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ከአንድ ክላስተር በላይ መወዳደር አይችሉም፤ እንዲሁም ሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች ደግሞ ከሁለት ክላስተር በላይ መወዳደር አይችሉም።
- ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ስራውን ያላጠናቀቀና ውሉ የተቋረጠ የግልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ስነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አሰራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲ/መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በ6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 046-2-12-84-46
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
