የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይ/ዓለም ከተማ አስ/ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት አጠቃላይ የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ ከሕጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይ/ዓለም ከተማ አስ/ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይ/ዓለም ከተማ አስ/ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት አጠቃላይ የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ ከሕጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ፤
- ተጫራቾች ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከመንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉና እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GUARANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ቫት (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ደረሰኙን በመያዝ ከይ/ዓለም ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ከፍል የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ጋር ኦሪጅናል አንድ እና ሁለት ኮፒዎችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ዞን የይ/ዓለም ከ/አስ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የቢሮ ፈርኒቸሮቹን የምርት ናሙና /sample/ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
- ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0916 078 104 እና 0912 410 135 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የይ/ዓለም ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
