በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 002/2017 መሰረት ቋሚ እቃ/ጄኔሬተር ባለ 90 KB ፣ 60 KB በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 002/2017 መሰረት ቋሚ እቃ/ጄኔሬተር ባለ 90 KB ፣ 60 KB በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
- ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የሀገር ውስጥ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ ከነቫቱ መጠቀስ አለበት።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00-10፡00 ሠዓት በፋ/ግ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት በእያንዳንዱ ሎት 2% (ሁለት ፐርሰንት) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የግዢውን ግምታዊ ዋጋ 10% በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናውን ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፤ ካላቀረቡ ግን ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል።
- የሚቀርቡት ዕቃዎች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በግዥ ጨረታው ላይ ከተጠየቀው ውጪ ናሙና ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
ማሳሰቢያ ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ከኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ ጀርባ ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ ፡- 0113 20 28 13 ወይም 0113 72 77 68
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
