ከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማኅበር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 17 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በአይሲቲው ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ያገለገሉ ስድስት ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
KENERA INTERNATIONAL TRADING PVT. LTD (ከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማኅበር)
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2025
ከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማኅበር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 17 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በአይሲቲው ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ያገለገሉ ስድስት ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
የስሪት ዘመን |
የተሽከርካሪ ሞዴል |
|
1 |
Daihatsu Terios |
1998 |
E-J100G-GPDE |
|
2 |
TOYOTA Hiance Minibus D4D |
2005 |
Hiance D4D |
|
3 |
TOYOTA RAV4 |
2012 |
RAV4 |
|
4 |
Hyundai 1-10 |
2012 |
110 |
|
5 |
Hyundai 1-10 |
2012 |
110 |
|
6 |
Hyundai 1-10 |
2012 |
110 |
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሥራ ሰዓትየጨረታውን ሰነድ በነጻ ከድርጅቱ ዋና ቢሮ ቦሌ ጌቱ ኮሜርሽያል አካባቢ አምራን ሆቴል ጀርባ ዳሽን ባንክ ያለበት ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ከሚገኘው በመውሰድ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹ በሚገኙበት ደንበል ኦሎምፒያ የድርጅቱ ግቢ ውስጥ በመገኘት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 አስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ ዋጋ በጨረታው ሰነድ ሰንጠረዥ ውስጥ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ ጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ የድርጅቱ ዋና መቤት ቦሌ ጌቱ ኮሜርሽያል አካባቢ አምራን ሆቴል ጀርባ ዳሽን ባንክ ያለበት ሕንጻ 4ኛ ፎት ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
- በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አንድ ተሽከርካሪ 5 በመቶ 5% በከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ በግልጽ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተገለጸበት እለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ በመክፈል ተሽከርካሪውን መረከብ ይሮርበታል። በዚሁ መሠረት የማይፈጽም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱም ይሰረዛል።
- በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሚሆኑት ተጫራቾች የባለቤትነት ስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን በመፈጸም ተሽከርካሪውን ይረከባሉ።
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ/ የጨረታው አሸናፊዎች የሚፈለግባቸውን ክፍያ እንዳጠናቀቁ የሚመለስላቸው ሲሆን በጨረታው አሸናፊ ለሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ከቀሪው ክፍያ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች ስለሽያጩ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ 0989 808080 ወይም 0115545738 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የድርጅቱ ዋና ቢሮ ቦሌ ጌቱ ኮሜርሽያል አካባቢ ኣምራን ሆቴል ጀርባ ዳሽን ባንክ ያለበት ሕንጻ 4ኛ ፎቅ
