Tender Detail

Tender Details

  • Company Robe College of Teachers Education (የሮቤ መምህራን ኮሌጅ)
  • Address ባሌ ሮቤ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913223605
  • Websitehttps://www.rcte.edu.et/
  • Deadline27 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Wood And Wood Working

የሮቤ መምህራን ኮሌጅ በሮቤ ከተማ ሮቤ መምህራን ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉትን የፅድ እንጨቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Robe College of Teachers Education (የሮቤ መምህራን ኮሌጅ)


ሠመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የፅድ እንጨት ሽያጭ

 ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር KBR.3/2017

 

የሮቤ መምህራን ኮሌጅ በሮቤ ከተማ ሮቤ መምህራን ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉትን የፅድ እንጨቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር ወይም መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-

  1. የጨረታውን ሰነድ ከሮቤ መምህራን ኮሌጅ በመግዛት መሳተፍ ይችላል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኮሌጁ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ መሙላት አለባቸው፡፡ ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆነ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) በፊት ያለውን ዋጋ መሙላት አለበት፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብቻ በሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1072925211214 በመክፈል የከፈሉበትን የባንክ ደረሰኝ (Bank Deposit Slip) በመያዝ ከሮቤ መምህራን ኮሌጅ እቅድ ፣ ግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ) ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ስም እና ማህተም ወይም ግለሰብ ከሆነ የግለሰቡን ሙሉ ስም፣ ፊርማ እና ስልከ ቁጥር በመፃፍ ማስገባት አለበት፡፡
  6. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ በሁለት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና በማይከፈት ኮፒ ሆኖ በፖስታው ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ተፅፎ ማቅረብ አለበት፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት በሮቤ መምህራን ኮሌጅ እቅድ፣ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በማስገባት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3:45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ተወዳድሮ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው ቀን ያሸነፈበትን 10% በባንክ የተመሰከረ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በማስያዝ በአካል በመቅረብ ከኮሌጁ ጋር ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
  9. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 0913223605/0930292416/0930292419/0987263911 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የሮቤ  መምህራን  ኮሌጅ

 

Save Tender