Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address ደ/ብርሃን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline15 Feb 2025, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንከ አፄ ሚኒሊክ ቅርንጫፍ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ኤልያስ፤ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቁም እንሰሳት እርባታ ህብረት ስራ ማሕበር /8 ሰዎች/ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በደብረ ብርሃን ከተማ አስ/ጠባሴ ክ/ከ በቀድሞው አጠራር ቀበሌ 07 አስተዳደር ውስጥ ባለእግዚአብሄር ሰፈር የቁራሽ መሬት ልዩ መለያ ኮድ AM005070815007 የተመዘገበ ንብረት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


 

ለመጀመሪያ  ጊዜ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንከ አፄ ሚኒሊክ ቅርንጫፍ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ኤልያስ፤ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቁም እንሰሳት እርባታ ህብረት ስራ ማሕበር /8 ሰዎች/ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን በደብረ ብርሃን ከተማ አስ/ጠባሴ ክ/ከ በቀድሞው አጠራር ቀበሌ 07 አስተዳደር ውስጥ ባለእግዚአብሄር ሰፈር የቁራሽ መሬት ልዩ መለያ ኮድ AM005070815007 የተመዘገበ አዋሳኙ ከምስራቅ ባዶ ቦታ፣ ከምእራብ መንገድ፣ ከሰሜን አሸናፊ ሙላቱ፣ ከደቡብ ተ/ዮሀንስ ገ/አማኑኤል የሚያዋስኑት በወ/ሮ አለማየሁ ታለጌታ ፈለቀ ስም የተመዘገበውን በአፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 0143829 ላይ ለዋናው እዳ ብር 324,550.59 (ሶስት መቶ ሃያ አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ብር ከ59/100) ከጳጉሜ 03/2015 ዓ/ም ጀምሮ ተከፍሎ እስካለቀ ድረስ 8 ፐርሰንት ወለድ የሚከፈል ለአፈጻጸም ከሳሽ እንዲከፈል ለማስፈጸም በግምት መነሻ ዋጋ 2,568,810.31 (ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር 31/100 ) ብር ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

ስለዚህ ፡-

  1. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 08 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ እና የግምቱን 1/4ኛውን በፍ/ቤቱ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ለሃራጅ ባዩ በቅድሚያ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
  3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው እደፍርዱ ለማስፈጸም ነው።
  4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
  5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል::

 

በአብክመ  ጠቅላይ  ፍ/ቤት  የሰ/ሸዋ  ዞን  ከፍ/ፍ/ቤት

ደ/ብርሃን

Save Tender