የአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 - የጽዳት እቃዎች ግዥ ጨረታ፤ ሎት 2 - የታሸገ ውሃ ግዥ ጨረታ፣ ሎት 3 - የጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ ጨረታ፣ ሎት 4 - የተሽከርካሪ ጎማዎች እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ጨረታ፣ ሎት 5 -ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ግዥ ጨረታ እና ሎት 6- Air Conditioner (AC) ግዥ ጨረታ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች፦
የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- ACBO/NCB/G/01/2017
የአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 - የጽዳት እቃዎች ግዥ ጨረታ፤ ሎት 2 - የታሸገ ውሃ ግዥ ጨረታ፣ ሎት 3 - የጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ ጨረታ፣ ሎት 4 - የተሽከርካሪ ጎማዎች እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ጨረታ፣ ሎት 5 -ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ግዥ ጨረታ እና ሎት 6- Air Conditioner (AC) ግዥ ጨረታ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች፦
- በዘርፉ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና ታክስ ክሊራንስ (የታደሰ) እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት - 1 ብር 20,000.00፣ ለሎት - 2 ብር 10,000.00፣ ለሎት - 3 ብር 8,000.00፣ ለሎት - 4 ብር 10,000.00፣ ለሎት - 5 ብር 7,000.00 እና ለሎት - 6 ብር 15,000.00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከተሰጣቸው ባንኮች የተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአሶሳ ጉምሩከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በጨረታ መክፈቻው ዕለት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ መከፈቻ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
ለበለጠ መረጃ :- 057-4-48-30-74/057-4-48-31-44
አሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
