የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት -
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የወጡ የዕቃ/የአገልግሎት ግዥ
ሎት 1 የኮረሪማ አቅርቦት ግዥ
ሎት 2 የዛላ በርበሬ አቅርቦት ግዥ
ሎት 3 የባዮሜትሪክ ማሽን ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ለሎት 1 እና ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ እና ለሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
- ጨረታን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 22 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት የጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሻል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒከ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 እና ለሎት 2 ቴከኒካል ሠነድ ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60% ) ሲሆን ለሎት 3 ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን ሠነድ ግምገማ ውጤት (55%) እና የፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (45%) ድምር ውጤት 100 % አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ እና ስፔስፊኬሽን ሠነድ ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሻል እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹን በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 011 5 53 07 67/011 5 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
