በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ለ2017/2018 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የኤንፒ ኤስ ቦሮን እና ዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ከቦርከና ዩኒየን ከሚሴ ማዕከላዊ መጋዝን ወደ ወረዳ ለሚገኙ መሠረታዊ ሕብረት ሥራ ማህበራት መጋዘኖች ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮ/ብሄ/አስተ/ዞን ግብርና መምሪያ
የአፈር ማዳበሪያ ለመጓጓዝ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ለ2017/2018 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የኤንፒ ኤስ ቦሮን እና ዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ከቦርከና ዩኒየን ከሚሴ ማዕከላዊ መጋዝን ወደ ወረዳ ለሚገኙ መሠረታዊ ሕብረት ሥራ ማህበራት መጋዘኖች ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
ስለዚህ በሥራው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማኅበር /አ.ማ/ በአዲሱ አደረጃጀት የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ አጓጓዦች የማጓጓዣ ታሪፋችሁን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሠረት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታ መሳተፍ ትችላላችሁ። ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሴርትፍኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በጨራታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተሽከርካሪ ዝርዝር /ተ.ቁ ፣ የሴሌዳ ቁጥር ፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም /የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፊቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
አድራሻ ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 325 ኪ/ሜ ርቀት ተጉዘው ያገኙታል።
- የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱጋር ተያይዞ ይቀርባል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአሮ/ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ መምሪያ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በቦርከና ሁለገብ የገበሬዎች ኀ/ሥራ ማህበራት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ለ3 ወር የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ውል የሚፈጽሙ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ኦሮሞ ዞን ግብርና መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሠነዱን በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት የሚትችሉ ሲሆን፣ የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡01 ተዘግቶ የሚከፈተው በእለቱ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም በ16ኛ ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የመንግስት የሥራ ቀን 4፡01 ተዘግቶ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከሚሴ ከተማ ግብርና መምሪያ ግብርና ግብዓት ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335541737/0912453907/0910172480 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮ/ብሄ/አስተ/ዞን ግብርና መምሪያ
ከሚሴ
