በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቼይን ኤክስካቫተር ባለጃክ ሐመር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ስለሚፈልግ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር መከራየት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቲ 03-2017
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቼይን ኤክስካቫተር ባለጃክ ሐመር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ስለሚፈልግ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ግዥና አቅርቦት ቡድን በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው:: የጨረታ ሠነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ) ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በገንዘብ ያዥ በተፃፈ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ከሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይ በሌላ መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ከሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኦሪጅናል እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መመዝገብ የሚችለው የመሣሪያው ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪል ከሆነ ማስረጃ ያለው መሆን ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መመሪያ ውጭ የሚያቀርቡ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም ።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መንገድ አስተዳደር
የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ግዥና አቅርቦት ቡድን መሪ
ስልክ ቁጥር 0587713052/0911984416
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
