በ2017 በጀት ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎት መሠረት በዘርፉ ከተሰማሩ /ድርጅቶች/ ግለሰቦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በ2017 በጀት ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎት መሠረት በዘርፉ ከተሰማሩ /ድርጅቶች/ ግለሰቦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣
ሎት 3. የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ እና የአቅራቢነት ኤሌክትሪክ ኦን ላይን ምዝገባ /e-GP/ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት /VAT/ የተመዘገቡበትን ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የገንዘብ ምንጭ የሚያመለክት የባንከ ማስረጃ ከታወቀ ባንኮች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ የሥራ ቀናት የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በወረዳው ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ኦሪጅናል አንድ ፖስታ እና ኮፒውን በሁለት ፖስታ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦሪጅናል አንድ ፖስታ እና ኮፒውን በሁለት ፖስታ በማሸግ የፋይናንሻል ጨረታ ሰነድ ሞልተው በእያዳንዱ ገጽ ላይ ተፈርሞ ማህተም ተደርጎ በእናት ፖስታ በማጠቃለል ታሽጎ በመመሪያው መሠረት ሙሉ አድራሻ በመግለጽ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ6ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከ30 ደቂቃ በኃላ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ በመንግስት የሥራ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ መረጃ ዝርዝር ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቹ ወይም ወኪሉ በራሱ ፈቃድ በጨረታው ላይ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ከ2017 በጀት ዓመት በፊት በወረዳው ሥራ ወስዶ ያላስረከበ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- 09-10-50-31-78/ 09-78-76-89-42
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
