Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና ገጠር ልማት መምሪያ
  • Address ጎንደር ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0918730673
  • Website
  • Deadline21 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Transportation Service And Cargo

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2017/2018 ዓ.ም የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የኤንፒኤስ ቦሮን እና ዩሪያ በድምሩ = 82,784 ኩ/ል /ሰማኒያ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ሰማኒያ አራት ኩ/ል/ የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ካለው ደባርቅ ዩኒየን በስሩ ላሉ 31 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባለው 7 ወር ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና ገጠር ልማት መምሪያ


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2017/2018 ዓ.ም የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የኤንፒኤስ ቦሮን እና ዩሪያ በድምሩ = 82,784 ኩ/ል /ሰማኒያ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ሰማኒያ አራት ኩ/ል/ የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ካለው ደባርቅ ዩኒየን በስሩ ላሉ 31 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባለው 7 ወር ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች ፡-

  1. የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር /ቢሮ/ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑ የመንግሥት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  2. የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩ/ል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩ/ል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. የተሸከርካሪ ዝርዝር /ተ.ቁ/ የሰሌዳ ቁጥር የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2017 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ለሁለተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይቻላል፤
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በደባርቅ ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ቢሮ ቁጥር 204 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ28/4/2017 እስከ 12/5/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ በ13/5/2017 ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4:30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. አንድ ተጫራች በዩኒየኑ ውስጥ ከተዘረዘሩት ማኅበራት መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  12. መሥሪያ ቤቱ የሚያወዳድረው ለሁሉም መሠረታዊ ማኅበር በሚያቀርበው ጥቅል ድምር /ሎት/ ዋጋ ነው፡፡
  13. መምሪያው አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 207 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918730673 /0584171127 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና ገጠር ልማት መምሪያ

Save Tender