Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በአራዳ ከፍለ-ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም ሌሎች አላቂ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

    የጨረታ ቁጥር ብግጨ 002/17

 

በአራዳ ከፍለ-ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም ሌሎች አላቂ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም:-

እያንዳንዱ አቅራቢ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመገንዘብ የጨረታ ሰነዱን መስሪያ ቤታችን በግንባር በመቅረብ መግዛትና መወዳደር ይችላል፡፡

  1. ተጫራቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፤ በመንግስት ግዢ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና /orginal እና ቅጂ/ copy / ኤንቨሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት በቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል መግባት ይኖርበታል፡፡
  3. ተጫራቾች ናሙና ለማይቀርብባቸው ዕቃዎች አጭር መግለጫ /specification/ ማቅረብ አለባቸው::
  4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በcpo ከዋናው (orginal) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት መስሪያ ቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20 /ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የእቃ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ ያህል በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05

ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት

ስልክ :- 0111114800

አራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት

 

በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender