በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ ለሚያስፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም ላፕቶፕ፣ የዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ታብሌት ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ ለሚያስፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም ላፕቶፕ፣ የዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ታብሌት ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ሰነዱ የሚሸጥበት ቦታው በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 418 ነው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው ለሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
- ይህ ጨረታ በ16ኛው በሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻው ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- አቅራቢዎቹ የእቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ፎርም ላይ ነጠላ ዋጋውን እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይገባቸዋል፡፡ አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
