በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃ/ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል የራምፕ የድጋፍ ግንብ ሽንት ቤት የሻወር ቤት ሮቶ ስታንድ እና የዲች ግንባታ በግልፅ ጨረታ የሚገነቡ / B.C 9/ዘጠኝ /ለጥ/አ/ ማህበራት ብቻ ለግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃ/ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2017
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃ/ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል የራምፕ የድጋፍ ግንብ ሽንት ቤት የሻወር ቤት ሮቶ ስታንድ እና የዲች ግንባታ በግልፅ ጨረታ የሚገነቡ / B.C 9/ዘጠኝ /ለጥ/አ/ ማህበራት ብቻ ለግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የሚሠሩ የሥራ ዓይነቶችን ዝርዝር ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት የሚችሉ ሲሆኑ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መመዘኛዎችን እና የመወዳደሪያ መስፈርትና መጠይቆችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑ
- በመንግሥት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- በእጃቸው በአሁኑ ሰዓት ሥራ እንደሌላቸው ከዞኑ ኮንስትራክሽን እንዲሁም ከከተማ ኮንስትራክሽን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- በዞናችን ውስጥ የግንባታ ውል ያላቋረጡ የሚገልፅ ማስረጃ ከዞንና ከተማ ኮንስትራከሽን ማቅረብ የሚችል
- ለሚያስገቡት ለእያንዳንዱ ዋጋ የነጠላ ዋጋ መተንተኛ (Cost breakdown) ማቅረብ የሚችሉና የተሞላው ዋጋና (Rate) ከነጠላ ዋጋ መተንተኛው ጋር አንድ አይነት መሆኑን የሚጠበቅበት መሆኑን ማቅረብ የሚችል፣
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አጠቃላይ ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁ.22 ማቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሲፒኦ በባንክ የተመሰከረ ማቅረብና ማስያዝ
- የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነድ ፖስታ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት በቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አጠ/ ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁ.22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ላይ ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አጠ/ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁ.22 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት ይከፈታል።
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /Performance bond/ ለማስያዝ በሆስፒታሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7 /ሰባት/ የሥራ ቀናት ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ፤
- ጨረታው የሚከፈተው ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አጠ/ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁ.22 ሲሆን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0473312361 ያገኙናል።
