Tender Detail

Tender Details

  • Company Waliya Capital Goods Finance Business S.C (ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ቀበሌ 10 ከአጅፕ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ፀደይ ባንከ የሥልጠና፣ የጥናትና የምርምር ማዕከል ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 እና አዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ፒያሳ አትክልት ተራ ሴካ የንግድ ማዕከል ህንፃ ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 001 ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0920493114
  • Websitehttps://waliyacapital.com/
  • Deadline15 Jan 2025, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር ያገለገለና በጥሩ ሁኔታ የሚገኝ መኪና ባለበት የጃፓን ስሪት የሆነ TOYOTA Coaster Bus Brand 2019/2020 Model HZB70L-ZGMSS የሆነ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Waliya Capital Goods Finance Business S.C (ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር ያገለገለና በጥሩ ሁኔታ የሚገኝ መኪና ባለበት የጃፓን ስሪት የሆነ TOYOTA Coaster Bus Brand 2019/2020 Model HZB70L-ZGMSS የሆነ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የንብረቱን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በባህር ዳር ከተማ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 306 እንዲሁም በአዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ፒያሳ አትክልት ተራ ሴካ የንግድ ማዕከል ህንፃ ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 001 በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ በመጨመር እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን (መጫረቻውን/ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ማህበሩ ቢሮ ቁጥር 303 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው የጊዜ ገደብ መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.አ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተሽከርካሪው ያለበትን ሁኔታ ለማየት የሚፈልግ ተጫራች በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 10 በሚገኘው የድሮው አብቁተ/የአሁኑ ፀደይ ባንከ ግቢ በአካል በመገኘት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የተሽከርካሪ የሞተር ቁጥር፣ የቻንሲ ቁጥር፣ የሞዴል ሌሎች መረጃዎችን በአካል ካለው ጋር ዘወትር በስራ ሰዓት ማየትና ማረጋገጥ ይቻላል።
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው የመጨረሻ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 303 ከቀኑ 8፡00 ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቶች ለሽያጭ የቀረበው ተሽከርካሪ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ቦታ በቁጥርና በፊደል መሙላት አለባቸው በቁጥርና በፊደል የተሞላው ዋጋ ልዩነት ካለው በፊደል የተሞላው የሚያዝ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 220 5359 /058 220 6728 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. አድራሻ፡ ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ/ማ ባህር ዳር ቀበሌ 10 ከአጅፕ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ፀደይ ባንከ የሥልጠና፣ የጥናትና የምርምር ማዕከል ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ስልክ ቁጥር 0582205359/ 0582206728 እንዲሁም በአዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ፒያሳ አትክልት ተራ ሴካ የንግድ ማዕከል ህንፃ ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 001 ስልክ ቁጥር 0920493114 ይገኛል።

 

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender