Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033-2-20-10-62
  • Website
  • Deadline18 Jan 2025, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ፍ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ፍ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ፍ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ

  1. አላቂ የጽህፈት መሣሪያ፣
  2. ሌሎች አላቂ የጽዳት እቃዎች፣
  3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  4. ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
  5. የደንብ ልብስ
  6. ፋይል ፎልደር እና ሌሎች የህትመት ውጤቶችን ህጋዊ አቅራቢ የንግድ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፤
  4. ጠቅላላ የእቃው የግዥ መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  6. የሚገዙትን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከቦረና ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢ/ቁ. 3 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት የእቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒአ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ቦረና ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 15ኛው ቀን 8:30 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦረና ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በዚያው በተመሳሳይ ቀን በስራ ሰዓት በ8:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ9፡00 ሰዓት ላይ በቦረና ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ደጋፊ የስራ ሂደት ይከፈታል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ እና ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቦረና ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ/ቁ/ 033-2-20-10-62 ወይም 09-22-90-28-72 ላይ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉትን ዕቃ ቦረና ወረዳ ፍ/ቤት አጓጉዘው በአካል ማስረከብ ይጠበቅብዎታል፡፡
  14. አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ነው፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ፍ/ቤት

 

Save Tender