በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እየሰራ ላለው የተለያዩ የብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ለኦቨርሆሊንግና ለምርት ስራ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶችና ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሞቬኢኢ/ግጨሰ/02/2017
- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እየሰራ ላለው የተለያዩ የብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ለኦቨርሆሊንግና ለምርት ስራ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶችና ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
- ኢንዱስትሪው መግዛት የሚፈልጋቸው ግብዓቶችና እቃዎች ዝርዝር፡፡
|
ተ/ቁ |
የሎት ማጣቀሻ |
የእቃው ዓይነት |
መግለጫ |
|
1 |
ሎት 1 |
የፅሕፈት (Stationary) እቃዎች |
ብዛት በዝርዝር በዋናው ሰነድ ላይ ይገኛል። |
|
2 |
ሎት 2 |
የፅዳት እቃዎች |
|
|
3 |
ሎት 3 |
የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች (Safety Materials) |
|
|
4 |
ሎት 4 |
የኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
|
|
5 |
ሎት 5 |
ልዩ ልዩ የምርት አላቂ ግብዓቶች |
|
|
6 |
ሎት 6 |
የመስሪያ ፋሲሊቲ ፤ ቱልሶችና ማሽነሪ |
|
|
7 |
ሎት 7 |
ጥሬ ግብዓቶች |
|
|
8 |
ሎት 8 |
የቧንቧ እቃዎች |
|
|
9 |
ሎት 9 |
የኤሌክትሪካል እቃዎች |
|
|
10 |
ሎት 10 |
ሜካኒካል እቃዎች |
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በሟሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ (VAT) የተመዘገቡና (Tin No.) ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሎቱ ለቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር በዘርፉ ስራ ወይም ንግድ ላይ ስለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከዚህ ውጪ ተወዳድረው ቢገኙ ያስገቡት መወዳደሪያና ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመጫረቻውን ጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO) ማስያዝ ይኖሪባቸዋል፤ 2% (CPO) ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች 2% የጨረታ ማስከበርያ (CPO) ዋስትና የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፣ ለወደፊትም በኢንዱስትሪው ጨረታ አይሳተፉም ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ ያስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር መስፈር አለባቸው:: በዋጋው ላይ ማንኛውም ታክስና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ መገለፅ አለበት፡፡
- በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት እንዲኖረው ተደርጎ በነጠላ ዋጋው ተመስርቶ ጠቅላላ ዋጋው ይታረማል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው አንደኛው ቅጅ ላይ “ዋና” በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልከት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ በሁለቱ መካከል ያለመጣጣም ቢፈጠር “ዋና" ተብሎ ምልክት የተደረገበት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ማስፈር አለበት፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ከዚህ በላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግንባር ቀርበው ዝርዝር መረጃ የያዙ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤
- ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አምስት) የመንግስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የስራ መውጫ ባሉት ሰአቶች ሲሆን ጨረታው በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ተቋም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
- ኢንዱስትሪው ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Performance Bond) ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ቢሾፍቱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልከ ቁጥር (09 94 52 15 56 /09 36 65 65 77) ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ኢንዱስትሪው ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
ቢሾፍቱ
